Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 14:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ኢየሱስም ወዲያው እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፥ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ኢየሱስም ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጐደለህ፤ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ኢየሱስ ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ “አንተ እምነት የጐደለህ! ስለምን ተጠራጠርክ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፤ ስለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 14:31
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህም አብርሃም ያንን ቦታ “ጌታ ያዘጋጃል (ያህዌ ይርኤ)” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “ጌታ በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ።


በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፥ በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።


የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፥ ለራሱም የዘለዓለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፥


ነገር ግን የነፋሱን ብርታት አይቶ ፈራ፤ መስጠም በጀመረም ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ” ብሎ ጮኸ።


ወደ ጀልባዋ በወጡ ጊዜ ነፋሱ ፀጥ አለ።


ኢየሱስም ይህንን አውቆ እንዲህ አላቸው “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እንጀራ ስላልያዛችሁ ለምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?


እርሱም የእምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ “ከዚህ ወደዚያ ሂድ” ብትሉት ይሄዳል፤ የሚያቅታችሁ ምንም ነገርም የለም።


ነገር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም?


እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


ስለዚህም እርሱ ወደ ተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሣት፤ ትኩሳቱም ተዋት፤ ተነሥታም ታገለግላቸው ጀመር።


ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፥ “እፈቅዳለሁ፥ ንጻ” አለው።


እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፥ “ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር” ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል።


ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ፥ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ እንደነገራችሁ እዚያ ታገኙታላችሁ፥ ብላችሁ ንገሯቸው።”


“እንዲህ የምትፈሩት ስለምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው።


ከዚያም የልጅቱን እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም፥ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው።


እነርሱም “ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፥ ለስምዖንም ታይቷል” ይሉ ነበር።


ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ለአገልጋዮቹም ያዝናል። ኃይላቸውም እንደደከመ፥ የታሰረም ሆነ የተለቀቀ እንደሌለ ሲያዩ፥


እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው።


ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ተዘጋጅቶላችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች