Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 10:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ለሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ይሆኑበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 የሰው ጠላቶቹ፣ የገዛ ቤተ ሰዎቹ ይሆናሉ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ስለዚህ የሰው ጠላቶቹ፥ የገዛ ቤተሰቦቹ ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 10:36
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”


ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “ከአብራኬ የወጣ ልጅ ሕይወቴን ሊያጠፋት ከፈለገ፥ ይህ ብንያማዊ ቢያደርገው ምን ያስደንቃል? ስለዚህ ተዉት፤ ጌታ በል ብሎት ነውና ይራገም፤


ክፉ ነገር መጣበት፥ ከተኛበት ከእንግዲህ ወዲህ አይነሣም ይላሉ።


ጠላትስ ቢሰድበኝ፥ በታገሥሁ ነበር፥ የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ፥ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።


ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም ወንድሙን፥ ባልንጀራም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።


ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።”


የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።


ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፥ ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፥ ምራት በአማትዋ ላይ ትነሣለችና፤ የሰው ጠላቶች የቤቱ ሰዎች ናቸው።


ወንድም ወንድሙን፥ አባት ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ፤ ይገድሉአቸዋልም።


ጴጥሮስም “የእኔን እግር በጭራሽ አታጥብም” አለው። ኢየሱስም “ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ድርሻ የለህም፤” ብሎ መለሰለት።


ታላቅ ወንድሙ ኤሊአብ፥ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውካቸው? ዕብሪትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች