Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ይህ ሁሉ የሆነው ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው እንዲፈጸም ነው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይህም ሁሉ የሆነው ጌታ እንዲህ ሲል በነቢይ አማካይነት የተናገረው እንዲፈጸም ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 1:22
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ይገባዋል ብዬ የነገርኋችሁ ቃል ይህ ነው፤” አላቸው።


በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው እንዲፈጸም፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።


እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦


እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራ እንዲቀበል አስቀድሞም በነቢያት ሁሉ አፍ የተናገረውን እንዲሁ ፈጸመው።


ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል የጠበቅህ፥ በአፍህ እንደተናገርከው ሁሉ እነሆ ዛሬ በእጅህ ፈጸምከው።


ይህም “ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን እንኳን አላጠፋሁም” ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።


ይህም በነቢዩ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤ “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ፤”


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት፥ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፥ ይህም በመንግሥቱ ሁሉ በአዋጅና በጽሑፍ እንዲያስነግር ነው፤


ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን እኔ በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።


ነገር ግን በሕጋቸው ‘በከንቱ ጠሉኝ’ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።


መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥


በራሱ ሥር የለውም፤ ነገር ግን ለትንሽ ጊዜ ይቆያል፥ በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በመጣ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።


ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤


ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ፥ ይህም ከጌታ ዘንድ በነቢይ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” የተባለው እንዲፈጸም ነው።


ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ፤” የተባለው እንዲፈጸም ነው።


ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም።


የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የቅጣት ጊዜ ነውና።


የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ ዕቅዱን በአንድ ልብ እንዲያደርጉና መንግሥታቸውንም ለአውሬው እንዲሰጡ እግዚአብሔር በልባቸው አሳድሮአልና።


ይህም ወንጌል እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢያቱ አማካኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የሰጠው ተስፋ ነው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች