Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 9:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እርሱም፥ “የዚህ ዓይነቱ ሊወጣ የሚችለው በጸሎትና በጾም ብቻ ነው” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እርሱም፣ “የዚህ ዐይነቱ ሊወጣ የሚችለው በጸሎትና በጾም ብቻ ነው” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እርሱም “እንዲህ ዐይነቱ በጸሎትና [በጾም] ካልሆነ በቀር በሌላ በምንም አይወጣም።” ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 9:29
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትም ሠርቶ ከሆነ፥ ይቅር ይባላል።


እርሱም የእምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ “ከዚህ ወደዚያ ሂድ” ብትሉት ይሄዳል፤ የሚያቅታችሁ ምንም ነገርም የለም።


በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ እስከ መጨረሻው በጽናት ትጉ።


ይህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።


በድካምና በጥረት፥ በእንቅልፍ አልባ ሌሊቶች፥ በራብና በጥም፥ ብዙ ጊዜም በመራብ፥ በብርድና በመታረዝ አሳልፌለሁ።


በዚያም ጊዜ ሄዶ ከእርሱ የባሱ ክፉ ሌሎች ሰባት መናፍስትን ከእርሱ ጋር ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ የዚያም ሰው ሁኔታ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ይሆናል።”


ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የቀረሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።


በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።


ከዚያ ይሄድና ከእርሱ የከፉ ሰባት ሌሎች አጋንንትን ከእርሱ ጋር ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ የሰውየው መጨረሻ ከፊተኛው ይልቅ የከፋ ይሆናል። ለዚህም ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።”


በመገረፍ፥ በመታሰር፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመራብ፥


እንዲህ ዓይነቱ በጸሎትና በጾም ካልሆነ በቀር ከቶ አይወጣም።


ኢየሱስ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው፥ “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።


ከዚያም ተነሥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ ኢየሱስም ያሉበትን ስፍራ ማንም እንዲያውቅ አልፈለገም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች