Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 9:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ኢየሱስ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው፥ “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ወደ ቤት ከገባም በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ቀርበው፣ “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ኢየሱስም ወደ ቤት በገባ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ፦ “ለመሆኑ ይህን ርኩስ መንፈስ እኛ ልናስወጣው ስለምን አልቻልንም?” ብለው ለብቻው ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ “እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው?” ብለው ብቻውን ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ፦ እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው? ብለው ብቻውን ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 9:28
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ጠየቁት።


ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀመዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።


ብቻውንም በሆነ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር በዙሪያው የነበሩት ስለ ምሳሌው ጠየቁት።


ጴጥሮስም መልሶ “ይህንን ምሳሌ ተርጉምልን” አለው።


በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ትርጒም ንገረን፤” አሉት።


ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ለምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ?” አሉት።


ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ፤ በቤት ውስጥ እንዳለም ተሰማ።


ከዚያም ወደ ቤት ገቡ፤ ምግብ መመገብ እንኳ እስኪያቅታቸው ድረስ እንደገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።


ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሣው፤ ልጁም ተነሥቶ ቆመ።


እርሱም፥ “የዚህ ዓይነቱ ሊወጣ የሚችለው በጸሎትና በጾም ብቻ ነው” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች