Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 14:70 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

70 እርሱ ግን አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፥ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፥ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፥ በእርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

70 እርሱ ግን አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፣ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፣ በርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

70 እርሱ ግን እንደገና ካደ። ጥቂት ቈየት ብሎም በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፥ “የገሊላ ሰው መሆንህን በእርግጥ አነጋገርህ ያስረዳል፤ ስለዚህ በእርግጥ አንተም ከእነርሱ ወገን ነህ፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

70 እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን “የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

70 እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን፦ የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 14:70
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ግን፥ “የምትዪውን አላውቅም፤ አይገባኝምም” በማለት ካደ። ከዚያም ወደ መግቢያው በር ወጣ፤ በዚህ ጊዜ ዶሮ ጮኸ።


ገረዲቱም ባየችው ጊዜ እዚያ ለቆሙት፥ “ይህ ሰው ከእነርሱ አንዱ ነው” ብላ እንደገና ተናገረች።


እርሱ ግን፥ “እናንተ የምትሉትን ሰው እኔ አላውቀውም” እያለ ይምል ይገዘት ጀመር።


ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ “እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?


እስቲ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ታዲያ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ ይዘው እዚያው መሻገርያው ላይ ይገድሉታል፤ በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች