ማርቆስ 14:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 ወዲያው እየተናገረ ሳለ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ አብረውትም ሰይፍና ዱላ የያዙ፥ ከካህናት አለቆች፥ ጸሐፍትና ከሽማግሌዎች የተላኩ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም43 ወዲያው እየተናገረ ሳለ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ዐብረውትም ሰይፍና ዱላ የያዙ፣ ከካህናት አለቆች፣ ከጸሐፍትና ከሽማግሌዎች የተላኩ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 ወዲያውም ኢየሱስ ይህን ሲናገር ሳለ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱ ከካህናት አለቆች፥ ከሕግ መምህራን፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ የተላኩ ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 ወዲያውም ገና ሲናገር ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 ወዲያውም ገና ሲናገር ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ። ምዕራፉን ተመልከት |