Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለ ጦርነትና ስለ ጦርነት ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለ ጦርነትና ጦርነትን የሚያናፍስ ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በአቅራቢያችሁ ጦርነት ሲደረግና በሩቅም የጦርነትን ወሬ ስትሰሙ አትደንግጡ፤ ይህ ሁሉ ሊሆን ግድ ነው፤ ይሁን እንጂ መጨረሻው ገና ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 13:7
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።


ክፉ ዜናን አይፈራም፥ ልቡ የጸና፥ በጌታም የታመነ ነው።


ሠራዊትም ቢከብበኝ ልቤ አይፈራም፥ ጦርነትም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።


ድንገት ከሚያስፈራ ነገር፥ ከሚመጣውም ከኀጥኣን ጥፋት አትፈራም፥


“እነዚህ ሰዎች፤ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፤ ማንኛውንም ነገር፤ ‘አድማ’ አትበሉ፤ እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤ አትሸበሩለትም።


በምድሪቱም ከሚሰማው ወሬ የተነሣ ልባችሁ የዛለ አይሁን አትፍሩም፤ በአንዱም ዓመት አንድ ወሬ፥ በሚቀጥለውም ዓመት ሌላ ወሬ ይመጣል፥ በምድሪቱም ላይ ዓመጽ ይሆናል፥ ገዢም በገዢ ላይ ይነሣል።


“ከማሰናከያው የተነሣ ዓለም ወዮላት፤ ማሰናከያ ግድ ይመጣልና፤ የማሰናከያ ማምጫ ምክንያት የሆነው ያ ሰው ግን ወዮለት!


ንጉሡ ሄሮድስ ሰምቶ ታወከ፤ መላዋ ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከች፤


ብዙዎች፥ “እኔ እርሱ ነኝ” እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።


“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።


ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይታወክ፤ አይፍራም።


ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ “ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ይል ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች