Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ወንጌል ለዓለም ሕዝብ ሁሉ መዳረስ ይገባዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 13:10
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥቱ ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል።


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።


በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤


ይህም ወንጌል ወደ እናንተ ደርሶአል፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ካወቃችሁበት ቀን ጀምሮ፥ በእናንተ መካከል እንደ ሆነው እንዲሁ በመላው ዓለም ፍሬ ያፈራል፤ ያድጋልም።


ነገር ግን አልሰሙም ወይ? እላለሁ፥ በእርግጥም ሰምተዋል፤ “ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።”


እንዲህም አላቸው፤ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤


በምልክትና በድንቅ ሥራ ኃይል፥ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል፥ ከኢየሩሳሌም ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርሁ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ።


እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ስለ ሁላችሁም በመጀመሪያ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።


የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች