Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 10:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ደቀ መዛሙርቱም ይበልጥ በመገረም፥ “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ደቀ መዛሙርቱም ይበልጥ በመገረም፣ “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ደቀ መዛሙርቱም በጣም ተገረሙና፥ “ታዲያ በዚህ ሁኔታ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው “እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው፦ እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል? ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 10:26
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ፤” አሉት።


እንደ እብድ ሰው እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣቸዋለሁ፤ በሥራ ብዙ ደክሜአለሁ፥ ብዙ ጊዜ ታስሬለሁ፥ ብዙ ግርፋት ደርሶብኛል፥ ብዙ ጊዜ እስከ መሞት ደርሻለሁ።


ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፥ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳን አድርጓል” አሉ።


እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ፀጥ አለ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤


የሰሙትም “እንግዲህ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።


አንድ ሰውም “ጌታ ሆይ! የሚድኑ ጥቂቶች ናቸውን?” አለው። እርሱም እንዲህ አላቸው፦


ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀለዋል።”


ኢየሱስም አያቸውና፥ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች