Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሚልክያስ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ሰርቃችሁኛል። እናንተም፦ እንዴት እንሰርቅሃለን? ብላችኋል። በአሥራትና በቁርባን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ትሰርቁኛላችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት እንሰርቅሃለን?’ ትላላችሁ። “ዐሥራትና መባ ትሰርቁኛላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰው የእግዚአብሔርን ሀብት ይዘርፋልን? ሆኖም እናንተ እኔን ዘርፋችኋል፥ እናንተ ግን እንዴት ከአንተ እንዘርፋለን ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ ከእኔ የዘረፋችሁት ዐሥራትንና መባን ባለመክፈላችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚልክያስ 3:8
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም “የቄሣር ነው” አሉት። እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” አላቸው።


ኢየሱስም፥ “የቄሣርን ለቄሣር፥ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው። እነርሱም በእርሱ ተደነቁ።


የስሙን ክብር ለጌታ አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ።


አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖቶችን የምትጠላ ቤተ መቅደሶችን ትዘርፋለህን?


ለሁሉ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።


እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው።


“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።


እስራኤል ኃጢአት ሠርቶአል፤ ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥ ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።


“የታወረውን ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፥ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ይህንን ለገዢህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህንስ ይቀበላልን?” ይላል የሠራዊት ጌታ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ የሚሰርቅና በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእዚህ ላይ እንደተጻፈው ይጠፋል።


የተትረፈረፈም ፍሬ አብዝተው እንዲሰጡዋችሁ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


በልግስና የሚሰጥ ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፥ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።


ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፤ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቁርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣንም አላደከምሁህም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች