Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሚልክያስ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዜ ርቃችኋል፥ አልጠበቃችሁትምም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው እንዴት ነው? ብላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘የምንመለሰው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሕጌ ርቃችኋል፤ አልጠበቃችሁትምም። ‘ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’፥ እናንተ ግን ‘ወደ አንተ የምንመለሰው በምን ዐይነት ነው?’ ትላላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚልክያስ 3:7
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።”


ስለ እስራኤል ግን “ወደማይታዘዝና ወደሚቃወም ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ይላል።


የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።


ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና በደልዋን ትሸከማለች፤ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ሕፃኖቻቸውም ይፈጠፈጣሉ፥ እርጉዞቻቸውም ይቀደዳሉ።


ዐሣማዎችም ከሚበሉት ፍልፋይ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ የሚሰጠውም አልነበረም።


“ከዳተኞች ልጆች ሆይ! ተመለሱ፥ ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ።” “እነሆ፥ አንተ አምላካችን ጌታ ነህና ወደ አንተ መጥተናል።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን!ወዮላችሁ፥ በውጫቸው አምረው የሚታዩ በውስጣቸው ግን በሙታን አጥንትና በርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ትመስላላችሁና።


“ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል።


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቆጣኝን ቁርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቁርባናቸውን አፈሰሱ።


ልጆች ግን ዐመፁብኝ፥ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርባትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጓትም በሥርዓቴም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም አረከሱ፤ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ ቁጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለሁ አልሁ።


ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቁጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


መልካም ባልሆነው መንገድ፥ አሳባቸውን እየተከተሉ፥ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ።


“ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ።


በእኔ ላይ የድፍረት ቃላትን ተናግራችኋል፥ ይላል ጌታ። እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድነው? ትላላችሁ።


ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።


እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።


አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በየዕለቱ እየማለድሁ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሜ ላክሁባችሁ።


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤


እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች