Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሚልክያስ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እኔ ጌታ አልለወጥምና፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ አልጠፋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ አልጠፋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ ስለዚህ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ገና ፈጽማችሁ አልጠፋችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፣ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚልክያስ 3:6
36 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘለዓለምም ያው ነው።


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ የሆንሁ ጌታ ነኝ፤ በውኑ ለእኔ የሚሳነኝ ነገር አለን?


የእስራኤል ክብር የሆነው እርሱ አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም።”


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ “አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፤” ይላል።


አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”


የእስራኤል ንጉሥ ጌታ፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ፥ እኔ ፍጻሜም ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።


የጌታ ጽኑ ፍቅር ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፥


አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።


በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽመው በዚህ እርግጠኛ ሆኛለሁ፤


እኔ አምላክህ ጌታ ነኝ፦ “አትፍራ፥ እረዳሃለሁ” ብዬ ቀኝህን የያዝኩ።


እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም ዳግመኛ አላጠፋም፤ በመዓትም አልመጣም።


ተመለሱም እንደ አባቶቻቸውም ከዱ፥ እንደ ጠማማ ቀስትም ተገለበጡ፥


እርሱ ግን ርኅሩኅ ነው፥ በደላቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፥ ከቁጣውም መመለስን አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም።


ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው።


ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤


እንዲህም አለው፦ “ጌታ፥ በራሴ እምላለሁ፥ ይላል፤ ምክንያቱም ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልከኝምና፤


በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥


እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፥ ሁላቸውም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጣሉም፥


ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው።


አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።


እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻችኋለሁ እኔም አነሣችኋለሁ፤ እኔ እሸከማችኋለሁ እኔም አድናችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች