Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሚልክያስ 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በመንጋው ውስጥ ተቀባይነት ያለው ተባዕት በግ ኖሮት ይህንኑ ሊሰጥ ተስሎ ሳለ፣ በማታለል ነውር ያለበትን እንስሳ ለጌታ የሚሠዋ ርጉም ይሁን፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ ሊፈራ የሚገባ ነውና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚልክያስ 1:14
39 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።


“የታወረውን ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፥ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ይህንን ለገዢህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህንስ ይቀበላልን?” ይላል የሠራዊት ጌታ።


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


የዚያ ባርያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፤ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርጋል።


“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።


ጌታም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን ጌታ አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።


ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፥ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ለሚያስፈራው እጅ መንሻን ያስገቡ።


አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።


አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


የተባረከና ብቻውን ገዢ የሆነ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ይህን ነገር ተገቢ በሆነው በራሱ ጊዜ ይገልጠዋል።


የጌታን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፥ ደም ከማፍሰስም ሰይፉን የሚከለክል ርጉም ይሁን።


ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የዚህን ሕግ ቃሎች በጥንቃቄ ባትከተልና አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የጌታ እግዚአብሔርን ስም ባታከብር፥


ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ፥ መርገምንም በላዬ አመጣለሁ፥ በረከትን አይደለም።”


እርሷ ማድረግ የምትችለውን ያህል አድርጋለች፤ ለመቃብሬ እንዲሆን ሰውነቴን አስቀድማ ቀብታለች።


ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


በምድርም አትማሉ የእግሩ ማረፊያ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አትማሉ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤


እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ ሰርቃችሁኛልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።


ጌታ ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።


ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፥ ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኃይሉም በደመናት ላይ ነው።


ጌታ ትልቅ ነው፥ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።


ንጉሡ ግን ኦርናን፥ “መክፈል ያለብኝን ዋጋ ላንተ ከፍዬ እንጂ እንዲሁማ አይሆንም፤ ለጌታም ለአምላኬ የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤


እኔ ሕያው በመሆኔ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ፥ በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል።


ወደ ሞአብና ከተሞችዋ አጥፊው ወጥቶአል፥ የተመረጡትም ጉልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ።


ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


“ካህናት ሆይ፥ አሁንም ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።


ጌታ ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።


እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፥ በጥበብ ዘምሩ።


አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች