Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሚልክያስ 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እናንተ ግን፦ “የጌታ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬውና ምግቡም የተናቀ ነው በማለታችሁ አረከሳችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እናንተ ግን የእግዚአብሔር ገበታ፣ ‘ርኩስ ነው’ ምግቡም፣ ‘የተናቀ ነው’ በማለት ታቃልላላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እናንተ ግን ‘የእግዚአብሔር መሠዊያ የረከሰ ነው’ ብላችሁ የተናቀ መሥዋዕት ባቀረባችሁ ጊዜ አረከሳችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፣ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፥ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚልክያስ 1:12
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህን በመፈጸምህ ግን፥ የጌታ ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፥ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።”


ከእንጨት የተሠራው መሠዊያ ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ነበር፥ ማዕዘኖቹ፥ እግሩና ግድግዳው ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ እርሱም፦ “ይህ በጌታ ፊት ያለ ገበታ ነው” አለኝ።


ወደ መቅደሴም ይገባሉ እኔን ለማገልገል ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴን ይጠብቃሉ።


እስራኤል ሆይ! በእኔ በረዳትህ ላይ በመነሣትህ ጠፍተሀል።


ከልጆችህ ማናቸውንም ለሞሌክ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ አትስጥ፥ በዚህም የአምላክህን ስም አታርክስ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ፤ ቅዱሱንም ስሜን ለማርከስ አባትና ልጅ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤


“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።


እናንተ ግን ከመንገዱ ተለይታችኋል፤ በሕግም ብዙዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊንም ቃል ኪዳን አፍርሳችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በሕዝቦች መካከል ይሰደባልና” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች