Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ሴቲቱም መደበቅ እንዳልቻለች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ በምን ምክንያት እንደ ዳሰሰችውና እንዴት ፈጥና እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ሴትዮዋም ሳትታወቅ መሄድ እንዳልቻለች በተረዳች ጊዜ፣ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ለምን እንደ ነካችውና እንዴት ወዲያው እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተናገረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ሴትዮዋም እንዳልተሰወረች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ወደ ኢየሱስ መጥታ በእግሩ ሥር ወደቀች፤ ከዚያም በኋላ ለምን እንደ ነካችውና እንዴት ወዲያውኑ እንደ ተፈወሰችም በሕዝቡ ሁሉ ፊት ገለጠች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ሴቲ​ቱም እን​ዳ​ል​ተ​ሰ​ወ​ረ​ላት ባየች ጊዜ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች ሄዳ ሰገ​ደ​ች​ለት፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በምን ምክ​ን​ያት ወደ እርሱ እንደ ቀረ​በ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ እንደ ዳሰ​ሰች ወዲ​ያ​ውም እንደ ዳነች ተና​ገ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፥ በምን ምክንያትም እንደ ዳሰሰችው ፈጥናም እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:47
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሴትዮዋም የተደረገላትን በማወቅዋ እየፈራችና እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ እውነቱንም ሁሉ ነገረችው።


ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ለእናንተ ያለው ፍቅር እጅግ ጨምሯል።


ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤


እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤


ለጌታ በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።


መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፤ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤


ሳሙኤል ጌታ ያለውን ነገር አደረገ። ቤተልሔም እንደደረሰም፥ የከተማዪቱ ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡ፥ እነርሱም “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ብለው ጠየቁት።


እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለች፤ እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል ጌታ። ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።


ዛልኩኝ እጅግም ደቀቅሁ፥ ከልቤ መጠበብ የተነሣ ጮኽሁ።


ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤


በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ፈጥነው ከመቃብሩ ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊነግሩ ሮጡ።


ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም መካከል ታበየ፤ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ።


እኔ ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረም፤ አሁን ግን ኤፍሬም ሆይ! አመንዝረሃል፥ እስራኤልም ረክሶአል።


እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፥ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።


ኢየሱስ ግን፦ “አንድ ሰው ዳስሶኛል፤ ከእኔ ኃይል መውጣቱን አውቄአለሁና፤” አለ።


እርሱም፦ “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች