Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ቆሙ፤ እርሱም፦ “አንተ ወጣት! ተነሥ እልሃለሁ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ኢየሱስም፣ “አንተ ጐበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደፊት ራመድ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ ቃሬዛውንም የተሸከሙት ሰዎች ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ቀር​ቦም ቃሬ​ዛ​ውን ያዘ፤ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትም ቆሙ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጐበዝ ተነሥ እል​ሃ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ የተሸከሙትም ቆሙ፤ አለውም፦ አንተ ጐበዝ፥ እልሃለሁ፥ ተነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:14
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።


ኢየሱስም “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤


ከዚህ በኋላ ኤልያስ በልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ተዘርሮ “ጌታ አምላኬ ሆይ! እባክህ ይህን ልጅ ከሞት አስነሣው!” ሲል ጸለየ።


“የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ የሞተውን ሕያው በሚያደርግ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት አምላክ ፊት ነው።


አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።


ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።


እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።


በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? ዕረፍቴ እስኪመጣ ድረስ፥ የአገልግሎቴን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።


ሰውም እንዲሁ ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም።


እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ያስነውራል።


ጌታም የኤልያስን ጸሎት ሰማ፤ የልጁም እስትንፋስ እንደገና ተመልሶለት ዳነ።


ከዚያም የልጅቱን እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም፥ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው።


ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፦ “አታልቅሽ፤” አላት።


የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ፥ ይናገርም ጀመረ፤ ኢየሱስም ጐልማሳውን ለእናቱ ሰጣት።


ስለ እርሱም የተነገረው ይህ ነገር በመላው ይሁዳ በዙሪያውም ባለው አገር ሁሉ ተሰራጨ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች