Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል፤” የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 መንፈስ ቅዱስም በአካላዊ ቅርጽ እንደ ርግብ በርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰማይም፣ “የምወድድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በዚያኑ ጊዜ “አንተ የተወደድክ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 መን​ፈስ ቅዱ​ስም የር​ግብ መልክ ባለው አካል አም​ሳል በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰ​ማ​ይም፥ “የም​ወ​ድህ፥ በአ​ን​ተም ደስ የሚ​ለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 3:22
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትእዛዙን እናገራለሁ፥ ጌታ አለኝ፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።”


እነሆ ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።


“እነሆ የመረጥሁት አገልጋዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ ፍርድንም ለአሕዛብ ያውጃል።


እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።


በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሏልና የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው።”


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።


ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየ፤


እነሆ፥ ከሰማያት ድምፅ ወጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


“የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ ተሰማ።


በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የገሊላ ከተማ ከሆነችው ከናዝሬት መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ።


ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፥ “ይህ የምወደው ልጄ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።


“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን! ሰላምም ደስ በሚሰኝባቸው ሰዎች መካከል በምድር ይሁን!” አሉ።


እርሱም፦ “ዛሬ ይህ በጆሮዎቻችሁ የሰማችሁት ጽሑፍ ተፈጸመ፤” ይላቸው ጀመር።


ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ “መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይም ሲኖር አየሁ።


አባት ሆይ! ስምህን አክብረው።” ስለዚህም “አከበርሁት፤ ደግሞም አከብረዋለሁ፤” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።


የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል። ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤


እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ልጁ መንግሥት አፈለሰን፤


በሰው ዘንድ ወደ ተናቀው፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደዚህ ሕያው ድንጋይ እየቀረባችሁ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች