Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 19:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል፤’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ደግሞም “ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን ‘የወንበዴዎች ዋሻ’ አደረጋችሁት” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 እንዲህም አላቸው፦ “ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 “ቤቴ የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላል የሚል ጽሑፍ አለ፤ እና​ንተ ግን የሌ​ቦ​ችና የቀ​ማ​ኞች ዋሻ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 19:46
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።


ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ ራሴ አይቻለሁ፥ ይላል ጌታ።”


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


የቤቱ ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ራስ ላይ በዙሪያው ያለው ስፍራ ሁሉ የተቀደስ ይሆናል። እነሆ፥ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።


ምስክርነትህ እጅግ የታመነ ነው፥ አቤቱ፥ ለረጅም ዘመን፥ ለቤትህ ቅድስና ይገባል።


“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”


“‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው።


ሲያስተምራቸውም፥ “ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል፥ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች