Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 19:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ጠላቶችሽም በዙርያሽ ቅጥር የሚሠሩበት፥ አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁብት ቀኖች ይመጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከብበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ጠላቶችሽ በዙሪያሽ ዐጥር ዐጥረውና ከበው፥ በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ቀን ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ጠላ​ቶ​ችሽ አን​ቺን የሚ​ከ​ቡ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ይከ​ት​ሙ​ብ​ሻል፤ ያስ​ጨ​ን​ቁ​ሻ​ልም፤ በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ንም ከብ​በው ይይ​ዙ​ሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 19:43
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ በአንቺ ላይ ምሽግ ይሠራል፥ ደለልም በአንቺ ላይ ይደለድላል፥ በአንቺም ላይ ጋሻ ያነሣል።


ክበባት፥ ምሽግም ሥራባት፥ ቁልልም ሥራባት፥ ሰፈርም አቁምባት፥ በዙሪያዋም ቅጥርን የሚያፈርስ ግንድ አድርግባት።


“ስለዚህም ጌታ ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም አይደለድልባትም።


ንጉሡም ተቆጣ፤ ወታደሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፥ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት።


“አንቺስ ለሰላምሽ የሚሆነውን ምነው በዚህ ቀን ባወቅሽ ኖሮ! ነገር ግን አሁን ከዐይንሽ ተሰውሮአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች