Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 17:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ቢጸጸትም ይቅር በለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። “ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ! ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው! በበደሉ ከተጸጸተም ይቅር በለው!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ወን​ድ​ምህ አን​ተን ቢበ​ድል ብቻ​ህን ምከ​ረው፤ ቢጸ​ጸት ግን ይቅር በለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 17:3
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።


በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባባት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤


መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።


ግልጽ ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።


ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ወንድሜ ስንት ጊዜ ቢበድለኝ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” አለው።


“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤


እንግዲህ ስለ አኗኗሯችሁ በጥንቃቄ ተጠበቁ፥ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው አይሁን፤


“ጌታ በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ ምንም መልክ አላያችሁምና፥ ለነፍሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ፤


ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ ጌታ አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም መልክ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


ከመካከላችሁ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት መራራ ሥር በቅሎ እንዳያስጨንቃችሁ፥


ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ አንዱ ከእውነት ቢስትና ሌላው ቢመልሰው፥


የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ነገር ግን ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች