Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 16:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ጌታውም አጭበርባሪውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ከመሰሎቻቸው ጋራ በሚኖራቸው ግንኙነት ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጌታ​ውም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ከብ​ር​ሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓ​ለ​ማ​ቸው ይራ​ቀ​ቃ​ሉና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 16:8
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት።


ነገር ግን አምኖን በጣም ዘዴኛ የሆነ፥ ዮናዳብ ተብሎ የሚጠራ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ነበር፤


ስለዚህም የበዓልን ነቢያት በሙሉ፥ በዓልን የሚያመልኩትንና ካህናቱን ጭምር በአንድነት ጠርታችሁ ሰብስቡልኝ፤ በምንም ምክንያት የሚቀር አይኑር፤ እኔ ለበዓል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ በዚያ የማይገኝ ማንም ሰው ቢኖር በሞት ይቀጣል።” ይህም ሁሉ በዓልን የሚያመልኩትን ሁሉ ለመግደል ኢዩ ያቀደው የተንኰል ዘዴ ነበር።


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


እንዳይበዙ፥ ጦርነትም በተነሣብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ ኑ በጥበብ እንምከር።”


ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ ግን በዚህ ዓለምም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።


እርሱም “ከሌሎች” አለው፤ ኢየሱስም “ስለዚህ ልጆች ነጻ ናቸው።


“በትንሹ የታመነ በብዙም እንዲሁ የታመነ ነው፤ በትንሹ የሚያታልል በብዙም እንዲሁ ያታልላል።


ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ፤’ አለ።


በኋላም ሌላውን ‘አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ፤’ አለው።


ጌታም አለ፦ “ዐመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም፤


ለሚመጣው ዓለምና ለሙታን ትንሣኤ ተገቢ የሆኑት ግን አያገቡም፤ አይጋቡምም፤


የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ፤” አላቸው። ኢየሱስም ይህን ከተናገረ በኋላ ሄዶ ተሰወረባቸው።


ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚህ ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው፥ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።


ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤


መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው ምድራዊ ነው።


እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፥ የቀንም ልጆች ናችሁና፤ ሆኖም እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ ይገለጣሉ፤ ጽድቅን የማያደርግ ሁሉ እና ወንድሙን የማይወድ ከእግዚአብሔር አይደለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች