Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 14:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 “ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፣ የራሱንም ሕይወት እንኳ ሳይቀር ባይጠላ፣ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 14:26
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጨርሶ ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።


እርሱም፦ “አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


ሌላውም ‘ሚስት አግብቼአለሁ፤ ስለዚህም ልመጣ አልችልም’ አለው።


ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤ ዘወር ብሎም እንዲህ አላቸው


ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘለዓለም ሕይወት ይጠብቃታል።


ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።


“ያዕቆብን ወደድሁ፥ ኤሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


“አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፤ አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥


ለአንት ሲል እናቱንና አባቱን፥ ‘አላየሁም’ ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ ልጆቹንም ላላወቀ፥ ቃልህን ላከበረ፥ ቃል ኪዳንህንም ለጠበቀ።


አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥


እነርሱም በበጉ ደምና በምስክራነታቸው ቃል ድል ነሡት፤ ሞትን እስኪሸሹ ድረስ ነፍሳቸውንም አልወደዱም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች