Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 14:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን ‘አሁን ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ኑ’ እንዲላቸው አገልጋዩን ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የግብዣውም ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን እንግዶች፣ ‘እነሆ፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷልና ኑ’ ብሎ እንዲጠራ ባሪያውን ላከባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ፥ ‘እነሆ፥ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ!’ ብሎ እንዲነግራቸው ጋባዡ አገልጋዩን ወደ ተጠሩት ሰዎች ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለምሳ የተ​ጠ​ሩ​በ​ትም ቀን በደ​ረሰ ጊዜ የታ​ደ​ሙ​ትን ይጠ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱም ሄዶ የታ​ደ​ሙ​ትን፦ አሁን ምሳ​ውን ፈጽ​መን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ና​ልና ኑ አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን፦ አሁን ተዘጋጅቶአልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 14:17
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ ሁሉ የሆነው፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን፥ የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው፤


እናንተ ወንድሞቻችን፥ የአብርሃም ዘር ልጆች ከእናንተ መካከልም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ! ለእናንተ የዚህ የመዳን ቃል ተላከ።


ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።


እርሱ ግን እንዲህ አለው “አንድ ሰው ታላቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን ጠራ፤


ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የመጀመሪያው ‘መሬት ገዝቼአለሁ፤ ወጥቼም ላየው የግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ፤’ አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች