Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 14:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰንበትም ቀን ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ሰንበት ቀን፣ ኢየሱስ ምግብ ሊበላ ከፈሪሳውያን አለቆች አንዱ ወደ ነበረ ሰው ቤት በገባ ጊዜ፣ ሰዎች በዐይን ይከታተሉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሰንበት ቀን፥ ኢየሱስ ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምሳ ሊበላ ገባ፤ ፈሪሳውያን እርሱ የሚያደርገውን ለማየት ይጠባበቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰንበትም ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 14:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም በሰንበት ይፈውሰው እንደሆነ አይተው ሊከስሱት ፈልገው ይጠባበቁት ነበር።


በቅርብ እየተከታተሉትም ለገዢው ግዛትና ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት ጻድቃን መስለው በቃሉ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት።


ይህንንም በመናገር ላይ በነበረ ጊዜ አንድ ፈሪሳዊ ከእርሱ ጋር ምሳ እንዲበላ ለመነው፤ ኢየሱስም ወደ እርሱ ገብቶ ተቀመጠ።


እስከ መቼ በሰው ላይ ትነሣላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ።


ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ መቼ ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል? ይላሉ።


ጻፎችና ፈሪሳውያንም የሚከስሱበትን ምክንያት ሊያገኙበት በሰንበት ይፈውስ እንደሆነ ለማየት ይጠባበቁት ነበር።


በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፥ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም።


ክፉ ጻድቁን ይመለከተዋል፥ ሊገድለውም ይወድዳል።


ከፈሪሳውያንም ወገን አንድ ሰው ነበረ፤ ስሙ ኒቆዲሞስ ሲሆን የአይሁድም አለቃ ነበረ፤


ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፤


ታዲያ ከበግ ይልቅ ሰው እንዴት አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል።”


እነሆም፥ ሰውነቱ በሙሉ ያበጠበት ሰው በፊቱ ነበረ።


ፈሪሳውያንም “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?” ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ “የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች