Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወይንስ በሰሊሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወይም ደግሞ በሰሊሆም ግንብ ተንዶባቸው የሞቱት ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ በደለኞች ስለ ነበሩ ይመስላችኋል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው ስለሞቱት ዐሥራ ስምንት ሰዎች ምን ታስባላችሁ? እነርሱ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የባሱ ኃጢአተኞች የነበሩ ይመስሉአችኋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወይስ እነ​ዚያ በሰ​ሊ​ሆም ግንብ ተጭኖ የገ​ደ​ላ​ቸው ዐሥራ ስም​ንቱ ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎች ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​እ​ታ​ኞች ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 13:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።


የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ።


እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”


“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፤ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።


መተሳሰብ በጀመረ ጊዜ፥ አስር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።


እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


ኀጢአታችንንም ይቅር በለን፤ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር እንላለንና፤ ወደ ፈተናም አታግባን።’ ”


“አይደለም”፤ እላችኋለሁ፥ “ነገር ግን ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


ነገር ግን ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁም እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።”


እርሱ መልሶ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ፤’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ፤” አለ።


“ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ፤” አለው፤ ትርጓሜውም “የተላከ” ማለት ነው። ስለዚህም ሄዶ ታጠበ፤ እያየም መጣ።


አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች