Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ የምትደረጊ ይመስልሻልን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንቺም ቅፍርናሆም፤ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ልትዪ ነውን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንቺም ቅፍርናሆም! እስከ ሰማይ ከፍ ለማለት ፈልገሻልን? ታዲያ ወደ ሲኦል ትወርጂአለሽ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አን​ቺም ቅፍ​ር​ና​ሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወ​ር​ጃ​ለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 10:15
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም ክልል ወደ አለችው በባሕር አጠገብ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።


እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥


አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን፥ ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት እያያችሁ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ በቆየች ነበር።


ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ።


እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


ከወደቁ ኃያላን ካልተገረዙ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ ሰይፋቸውንም ከራስጌያቸው በታች አድርግው ወደ ሲኦል ከወረዱ ጋር አልተኙም፥ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ነበር


በሰይፍ በተገደሉት መካከል ይወድቃሉ፤ ለሰይፍ ተሰጥታለች፤ እርሷንና ብዛትዋን ሁሉ ጐትቱ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ብዛት ዋይ በል፥ እርሷንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።


በክብርና በታላቅነት ከዔድን ዛፎች መካከል እንግዲህ ማንን ትመስላለህ? ሆኖም ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ትወርዳለህ፥ በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትጋደማለህ። ይህም ፈርዖንና ብዛቱ ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የጥንት ሕዝብ ወዳሉበት ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፥ የሚኖርብሽም እንዳይገኝ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ቀድሞ በፈረሰችው ስፍራ፥ በታችኛይቱ ምድር አኖርሻለሁ፤ ጌጥሽንም በሕያዋን ምድር አላኖርም።


ምንም እንኳ ባቢሎን ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ የኃይልዋንም ከፍታ ብታጠናክር፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል ጌታ።


ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፤ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤ መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋር ወደዚያ ይወርዳሉ።


ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት።


እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።


በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ፥ አልዓዛርንም በእቅፉ አየ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች