ዘሌዋውያን 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ሙሴም አሮንን፦ “ወደ መሠዊያው ቅረብ፥ የኃጢአትህንም መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ ጌታም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቁርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሙሴ አሮንን፣ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአት መሥዋዕትህንና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት የሕዝቡን መሥዋዕት አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ከዚህም በኋላ ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፤ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የራስህን ኃጢአትና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ፤ ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አቅርብ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሙሴም አሮንን፥ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለወገንህ አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ሙሴም አሮንን፦ ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም አለው። ምዕራፉን ተመልከት |