Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አሮንንም እንዲህ አለው፦ “ከመንጋው ነውር የሌለባቸውን ለኃጢአት መሥዋዕት እምቦሳውን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ወስደህ በጌታ ፊት አቅርብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አሮንንም እንዲህ አለው፤ “የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ እንቦሳ እንዲሁም የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ አውራ በግ ወስደህ፣ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ ሁለቱም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አሮንንም እንዲህ አለው፤ “ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ የበግ አውራ ወስደህ ወይፈኑን ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ የበግ አውራውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሙሴም አሮ​ንን አለው፥ “ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋው እን​ቦ​ሳ​ውን፥ ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አው​ራ​ውን በግ ወስ​ደህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሮንንም አለው፦ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እምቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ነውር የሌለባቸውን ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 9:2
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለእኔ ካህናት እንዲሆኑ እንድትቀድሳቸው የምታደርገው ነገር ይህ ነው፤ አንድ ወይፈንና ነውር የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ።


በአሥረኛው ዓመት፥ በአሥረኛው ወር ከወሩም በዓሥራ ሁለተኛው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


“የእርሱም ቁርባን ለሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል።


“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።


ነገር ግን አሮን ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀደሰ ስፍራ ይግባ።


ከእስራኤልም ልጆች ማኅበር ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለት አውራ ፍየሎች፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።


የተቀባውም ካህን ኃጢአት ሠርቶ በሕዝቡ ላይ በደል ቢያመጣ፥ ስለ ሠራው ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለጌታ ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል።


የኃጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኃጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።


ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።


ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፦ ‘ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥


እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል።


እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች