Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 7:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ከአሮንም ልጆች መካከል የአንድነትን መሥዋዕት ደሙንና ስቡን ለሚያቀርበው ለእርሱ ቀኝ ወርቹ ድርሻው ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ሥብ የሚያቀርበው የአሮን ልጅ ቀኝ ወርቹን የራሱ ድርሻ አድርጎ ይውሰድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የቀኙ ወርች የአንድነቱን መሥዋዕት ደምና ስብ ለሚያቀርበው ካህን ድርሻ ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ከአ​ሮ​ንም ልጆች የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደሙ​ንና ስቡን ለሚ​ያ​ቀ​ርብ ለእ​ርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈን​ታው ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ከአሮንም ልጆች የደኅንነትን መሥዋዕት ደሙንና ስቡን ለሚያቀርብ ለእርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈንታው ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 7:33
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስቡንም ሁሉ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ያቀርበዋል።


ከሰላም መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን እንደ ቁርባን አድርጋችሁ ለካህኑ ትሰጡታላችሁ።


የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ።


ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፥ “ይህ፥ እንግዶችን ጋብዣለሁ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ፥ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች