Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 7:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለጌታ የአንድነትን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቁርባኑን ለጌታ ከሰላሙ መሥዋዕት ያመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ስለ ራሱ መሥዋዕት አድርጎ ከዚሁ ላይ ለእግዚአብሔር ያቅርብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ማንም ሰው የአንድነት መሥዋዕት ቢያቀርብ ከእርሱ ከፍሎ ለእግዚአብሔር የተለየ መባ ያምጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ለእግዚአብሔር የደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቁርባኑን ለእግዚአብሔር ከደኅንነቱ መሥዋዕት ያመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 7:29
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


በመስቀሉም ደም ሰላምን በማድረግ በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በእርሱ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታርቋል።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፥ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ አገልጋይ ይመጣ ነበረ፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፥


“ሰው ለጌታ የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።


ስቡንም በፍርምባዎቹ ላይ አደረጉ፥ እርሱም ስቡን በመሠዊያው ላይ አቃጠለ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች