Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 6:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ለኃጢአት የሚሠዋው ካህን ይበላዋል፤ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ ባለው አደባባይ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 መሥዋዕቱንም የሚያቀርበው ካህን ይብላው፤ ይህም በተቀደሰው ስፍራ በመገናኛው ድንኳን ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ በአደባባዩ ላይ ይበላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እንስሳውን የሚሠዋውም ካህን በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ባለው የተቀደሰ ስፍራ ይብላው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ለኃጢአት የሚሠዋው ካህን ይበላዋል፤ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ ባለው አደባባይ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 6:26
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን ተከለ፤ በአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ዘረጋ። በዚህ ዓይነት ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።


እንዲህም አለኝ፦ በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ ጌታ የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቁርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።


እንዲህም አለኝ፦ “ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቁርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው።”


የሕዝቤም ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፥ ልባቸውንም ወደ በደላቸው አዘንብለዋል።


ከእርሱም የተረፈውን አሮንና ልጆቹ ይበሉታል፤ እርሾ ያልነካው ቂጣ ሆኖ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል፤ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ ባለው አደባባይ ይበሉታል።


በእርሾ ቦክቶ አይጋገርም። እርሱን በእሳት የሚቀርብ ቁርባኔ አድርጌ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጠሁ፤ እርሱም እንደ ኃጢአትና እንደ በደል መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው።


ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእርሱ ይበላል፤ እጅግም የተቀደሰ ነው።


የበደል መሥዋዕት እንደ ኃጢአት መሥዋዕት ነው፤ ለሁለቱ አንድ ሕግ አለ፤ ያም በእነርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ከእነርሱ ላይ ለራሱ ስለ ሚወስድ ነው።


በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች