ዘሌዋውያን 6:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከልጆቹም መካከል በአባቱ ፋንታ የተቀባው ካህን ያዘጋጀዋል። ለዘለዓለም ሥርዓት እንዲሆን ፈጽሞ ለጌታ ይቃጠላል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በርሱ ቦታ ተቀብቶ ካህን የሚሆነው ልጁ ይህን ያዘጋጅ፤ ለእግዚአብሔር የተመደበ ድርሻ ነውና ፈጽሞ ይቃጠል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ከአሮን ተወላጆች መካከል ተቀብቶ የክህነትን ሥልጣን የሚረከብ ያን ያዘጋጃል፤ ያም የእግዚአብሔር ቋሚ ድርሻ ስለ ሆነ በሙሉ መቃጠል አለበት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ከልጆቹም በእርሱ ፋንታ የተቀባው ካህን ያቀርበዋል። ለዘለዓለም ሥርዐት ነው፤ ሁልጊዜም ይደረጋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ከልጆቹም በአባቱ ፋንታ የተቀባው ካህን ያቀርበዋል። ለዘላለም ሥርዓት እንዲሆን ፈጽሞ ለእግዚአብሔር ይቃጠላል። ምዕራፉን ተመልከት |