Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ለጌታ በእሳት ከሚቀረበው ቁርባን ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ድርሻቸው እንዲሆን ከአሮን ልጆች ወንዶቹ ሁሉ ይበሉታል። የሚነካቸው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ማንኛውም ከአሮን ዘር የተወለደ ወንድ ሊበላው ይችላል፤ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የእሳት ቍርባን ለርሱ የተመደበ የዘላለም ድርሻው ነው፤ የሚነካውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ትውልዱ ከአሮን ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ለእርሱ የተመደበለትን ፈንታ መብላት ይችላል፤ መባውን የሚነካ ሁሉ በቅድስናው ኀይል ይቀሠፋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከካ​ህ​ናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በዘ​መ​ና​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው። ከሚ​ቃ​ጠ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ለእግዚአብሔር ከቀረበ ከእሳት ቍርባን ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ እድል ፈንታቸው እንዲሆን ከአሮን ልጆች ወንዶቹ ሁሉ ይበሉታል። የሚነካቸው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 6:18
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰባት ቀን ለመሠዊያው ማስተስረያ ታደርጋለህ፥ ትቀድሰዋለህም፤ መሠዊያውም ፍጹም ቅዱስ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።


በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ ፈጽሞ ማንኛውንም ስብና ደም እንዳትበሉ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።”


በፍየሉም ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በጌታ ፊት ያርደዋል፤ እርሱ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።


የተቀባውም ካህን ኃጢአት ሠርቶ በሕዝቡ ላይ በደል ቢያመጣ፥ ስለ ሠራው ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለጌታ ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል።


እጁንም የኃጢአት መሥዋዕት በሆነችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መሥዋዕት ያርዳታል።


ካህኑም ሰውነቱን ለመሸፈን የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦


ሥጋውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል፤ በልብስ ላይ ደሙ ከቶ ከተረጨ የተረጨበትን በተቀደሰ ስፍራ ታጥበዋለህ።


ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእርሱ ይበላል፤ እጅግም የተቀደሰ ነው።


ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።


እጅግ በተቀደሰ ስፍራ ብላው፤ ወንዶች ሁሉ ይብሉት፤ ለአንተም የተቀደሰ ይሆንልሃል።


ጌታም አሮንን ተናገረው እንዲህም አለው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የቀደሱትን እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባኔን ሁሉ ለአንተ እንድትጠብቀው ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተና ለልጆችህ የክህነትህ ድርሻ እንዲሆን ለአንተ የተገባህ አድርጌ ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ።


በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?


ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ፤” ተብሎ ተጽፎአልና፤


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች