ዘሌዋውያን 27:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የግምቱን ዋጋ ያሰላለታል፤ በዚያም ቀን ግምቱን እንደ ተቀደሰ ነገር ለጌታ ይሰጣል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ካህኑ የዕርሻውን መሬት ዋጋ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ መጠን ይተምናል፤ ሰውየው የተተመነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ አድርጎ በዚያ ዕለት ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ካህኑ ገምግሞ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ያለውን ዋጋ ይተምን፤ ሰውየውም በዚያኑ ዕለት ዋጋውን ይክፈል፤ ገንዘቡም ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የግምቱን ዋጋ ይቈጥርለታል፤ በዚያም ቀን ግምቱን እንደ ተቀደሰ ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጣል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የግምቱን ዋጋ ይቈጥርለታል፤ በዚያም ቀን ግምቱን እንደ ተቀደሰ ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጣል። ምዕራፉን ተመልከት |