Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 26:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የእንጀራችሁንም በትር በሰበርሁ ጊዜ፥ ዐሥር ሴቶች እንጀራችሁን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው ዳግመኛ እንጀራችሁን ያመጡላችኋል፤ ትበላላችሁም ነገር ግን አትጠግቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የእንጀራችሁ እህል እንዲቋረጥ በማደርግበት ጊዜ፣ ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፤ እንጀራውንም በሚዛን መዝነው እናንተም ትበላላችሁ፤ ግን አትጠግቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ምግብ እንድታጡ በማደርግበት ጊዜ እንጀራችሁን ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፤ ምግባችሁንም መጥነው ያቀርቡላችኋል፤ እናንተም በልታችሁ አትጠግቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የእህላችሁንም ድጋፍ በሰበርሁ ጊዜ፥ አሥር ሴቶች እንጀራቸውን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው እንጀራችሁን ይመልሱላችኋል፤ በበላችሁም ጊዜ አትጠግቡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 26:26
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ባዶነትህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን ወደ ደህንነት አታመጣም፥ ወደ ደህንነት ያመጣኸውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ።


እነሆ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፉንና ርዳታውን፤ የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤


የሚገድሉና የሚያጠፉ የራብ ፍላፃ በወረወርሁ ጊዜ፥ እንዳጠፋችሁ እወረውራቸዋለሁ፥ በእናንተ ላይ ረሃብን እጨምርባችኋለሁ፥ የምግባችሁንም በትር እሰብራለሁ።


በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር ባለመታመን በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እጄን እዘረጋባታለሁ፥ የምግቧንም በትር እሰብራለሁ፥ ራብን እሰድድባታለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ አጠፋለሁ፤


ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ እኔ በኢየሩሳሌም የምግብን በትር እሰብራለሁ፥ ምግብ እየፈሩ በሚዛን ይበላሉ፥ ውኃም እየደነገጡ በልክ ይጠጣሉ፤


ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


እነርሱም ይበላሉ አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ አይበዙም ምክንያቱም ጌታን ትተው


የምትመገበውም ምግብ በሚዛን በየቀኑ ሃያ ሰቅል ይሁን፥ በየጊዜውም ትበላለህ።


በጾሙ ጊዜ ልመናቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ ይልቁንም በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ” አለኝ።


“ይህም ተደርጎባችሁ እንኳ ባትሰሙኝ፥ እኔንም በመቃወም ብትሄዱ፥


ከበባውም የምግብን እጥረትና ብርቱ ራብ ከማስከተሉ የተነሣ፥ የአንድ አህያ ራስ ዋጋ እስከ ሰማኒያ ጥሬ ብር፥ ሁለት መቶ ግራም የሚያኽል የርግብ ኩስ ዋጋ ደግሞ አምስት ጥሬ ብር ማውጣት ጀመረ።


ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።


ይህም ምግብና ውኃን እንዲያጡ፥ እርስ በርሳቸውም እንዲደነቁ፥ በኃጢአታቸውም እንዲመነምኑ ነው።


በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤ በግራም በኩል ይበላሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች