Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 26:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጉልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም የተትረፈረፈውን ምርትዋን አትሰጥም፥ የምድሪቱም ዛፎች ፍሬያቸውን አይሰጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኀይላችሁ በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁ እህሏን፣ የምድሪቱ ዛፎችም ፍሬዎቻቸውን አይሰጡምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ምድራችሁ ሰብልን ዛፎቻችሁም ፍሬን ስለማይሰጡ በከንቱ ትደክማላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጕል​በ​ታ​ች​ሁም በከ​ንቱ ያል​ቃል፤ ምድ​ራ​ች​ሁም እህ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥም፤ የዱር ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጕልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም እህልዋን አትሰጥም፥ የምድርም ዛፎች ፍሬአቸውን አይሰጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 26:20
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፥ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።”


ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አክዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሀብ እጅግ ጸንቶ ነበር።


በስንዴ ፋንታ አሜከላ፥ በገብስም ፋንታ ኩርንችት ይውጣብኝ።” የኢዮብ ቃል ተፈጸመ።


ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት።


የዕርገት መዝሙር። ጌታ ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፥ ጌታ ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤ መሸሸጊያ ዐለትህንም አላሰብክም፤ ስለዚህ ያማረውን ተክል ብትተክልም እንግዳንም ዘር ብትዘራ፥


በተከልክበት ቀን እንዲበቅል፥ በዘራህበት ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳን፥ ነገር ግን በኀዘንና በብርቱ ደዌ ቀን መከሩ እንዳልነበር ይሆናል።


እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ።


ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፤ እራሳቸውን አደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፤ ስለ ጌታ ጽኑ ቁጣ በፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።”


ስለዚህ እህሌን በጊዜው፥ ወይን ጠጄንም በወቅቱ ፈጽሞ እወስዳለሁ፥ ዕራቁትነትዋንም መሸፈኛ የነበረውን ጥጤንና የተልባ እግሬን እገፍፋታለሁ።


ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም የተትረፈረፈ ምርትዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።


እነሆ፥ አሕዛብ ለእሳት እንደሚሠሩ፥ ሕዝቦችም ለከንቱነት እንደሚደክሙ ከሠራዊት ጌታ ዘንድ የሆነ አይደለምን?


በዚያን ጊዜ አንድ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት መጣ፥ የተገኘው ግን ዐሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፤ አምሳ ማድጋ ለመቅዳት ወደ ወይን መጥመቂያው መጣ፥ የተገኘው ግን ሀያ ብቻ ነው።


እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤


ምናልባት ስለ እናንተ በከንቱ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።


የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”


“የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህ መንጋ፥ የበግና የፍየል መንጋ ይረገማሉ።


ዛፍህንና የምድርህን ሰብል ሁሉ ኩብኩባ ይወረዋል።


እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች