Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 24:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለጌታም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ተደርጎ፥ ለእንጀራው የመታሰቢያ ቁርባን እንዲሆን በሁለቱ ተርታ ላይ ንጹሕ የሆነ ዕጣን አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከኅብስቱ ጋራ የመታሰቢያ ድርሻ ሆኖ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት እንዲሆን ንጹሕ ዕጣን በእያንዳንዱ ረድፍ ላይ አኑር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በእሳት የሚቃጠል ለእግዚአብሔር የቀረበ የተቀደሰ ኅብስት ለመሆኑ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ንጹሕ የሆነ ዕጣን በሁለቱም ረድፍ ላይ አኑር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በሁ​ለ​ቱም ተራ ንጹሕ ዕጣ​ንና ጨው ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ለተ​ዘ​ጋ​ጁት ኅብ​ስ​ቶች ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለእግዚአብሔርም ለእሳት ቍርባን በእንጀራው ላይ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ በሁለቱ ተርታ ላይ ጥሩ ዕጣን አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 24:7
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ አሮንም ልጆች ወደ ካህናቱ ያመጣዋል። ከመልካም ዱቄቱና ከዘይቱ አንድ እፍኝ ሙሉና ዕጣኑን ሁሉ ከወሰደ በኋላ ካህኑ ለመታሰቢያ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


ለዚህም ነው፥ እነርሱን ሊያማልድ ዘወትር ይኖራልና፥ በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።


በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ።


‘ቆርኔሌዎስ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።


እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ “ጌታ ሆይ! ምንድነው?” አለ። መልአኩም አለው “ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።


እኔ ከሰማይ የወረደው ሕያው እንጀራ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም በፍጹም አይጠማም።


ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው።


በእጅህ እንደ ምልክት በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ፥ የጌታ ሕግ በአፍህ እንዲሆን፥ ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶሃልና።


ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።


ቀስቲቱም በደመና ስትሆን፥ አያታለሁም በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል ያለውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”


የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ ሁለቱን ዕንቁዎች በኤፉዱ ትከሻዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ ለመታሰቢያ እንዲሆን ስማቸውን በጌታ ፊት ይሸከማል።


ካህኑም ከእህሉ ቁርባን መታሰቢያውን አንሥቶ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፤ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቁርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣንም አላደከምሁህም።


“ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች