Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከእንጀራውም ጋር ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ሰባት ተባት ጠቦቶች፥ አንድ ወይፈንም፥ ሁለትም አውራ በጎች ታቀርባላችሁ። ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ሆኖ ከእህል ቁርባናቸውና ከመጠጥ ቁርባናቸው ጋር ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከእንጀራውም ጋራ ሰባት ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እንከን የሌለው ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች አቅርቡ፤ እነዚህም ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናሉ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከእንጀራውም ጋር ማኅበሩ ምንም ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰባት የበግ ጠቦቶች፥ አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ያምጡ፤ እነርሱም ከእህሉ ቊርባንና ከወይን ጠጁ መባ ጋር የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት ሆነው ይቀርባሉ፤ ይህም በእሳት የሚቀርበው መሥዋዕት ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከኅ​ብ​ስ​ቱም ጋር ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን የአ​ንድ ዓመት ሰባት ጠቦ​ቶች፥ ከመ​ን​ጋ​ውም አንድ ወይ​ፈን፥ ሁለ​ትም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው አውራ በጎች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸው፥ ወይ​ና​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከእንጀራውም ጋር ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ሰባት ጠቦቶች፥ አንድ ወይፈንም፥ ሁለትም አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሁኑ፤ ከእህልም ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ጋር ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የእሳት ቍርባን ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 23:18
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።


ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም ዱቄት የተሠራ ሁለት የመወዝወዝ እንጀራ ታመጣላችሁ። ለጌታ ለበኵራት ቁርባን እንዲሆን በእርሾ ተቦክቶ ይጋገራል።


እንዲሁም አንድ አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ለአንድነት መሥዋዕት አቅርቡ።


ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች