Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንዲህ ያሉትን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ነገር የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ሰውነቱንም በውሃ ካልታጠበ፣ የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ማንኛውም ሰው እነዚህን ነገሮች ቢነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውሃ ካልታጠበ በቀር የተቀደሱትን ነገሮች አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እነ​ዚ​ህን ሁሉ የሚ​ነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ገላ​ውን በውኃ ካል​ታ​ጠበ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እነዚህን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 22:6
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ መካከል፥ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


በድናቸውንም የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነርሱም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።


ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ መካከል በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሆኑት እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ከእነርሱም የሞተው በማናቸውም ነገር ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቆዳ ወይም ከረጢት ቢሆን ለማናቸውም ሥራ የሚጠቅም ዕቃ ሁሉ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ግን ይነጻል።


“ለምግብነት ከምታውሉት እንስሳ የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


መኝታውንም የሚነካ ማንም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም የሚርመሰመስ ፍጥረት፥ ወይም ርኩሰቱ ማናቸውም ዓይነት ሆኖ የሚያረክሰውን ሰው የሚነካ፥


ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ነገር ይበላል።


ሐጌም፦ በሬሳ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይረክሳልን? አለ። ካህናቱም፦ አዎን ይረክሳል ብለው መለሱ።


የረከሰውም ሰው የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።”


ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች