ዘሌዋውያን 22:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ይሁን እንጂ የካህኑ ልጅ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታ፣ ልጆችም ባይኖሯትና እንደ ልጅነት ጊዜዋ በአባቷ ቤት ለመኖር ብትመለስ፣ ከአባቷ ድርሻ መብላት ትችላለች፤ ያልተፈቀደለት ሰው ግን ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አይችልም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ነገር ግን ልጅ ሳትወልድ ባልዋ የሞተባት ወይም ከባልዋ በመፋታት ወደ አባቷ ቤት ተመልሳ መጥታ በጥገኝነት የምትኖር የካህኑ ልጅ በልጅነትዋ ታደርገው እንደ ነበረው ሁሉ የአባቷ ድርሻ ከሆነው ቅዱስ ነገር ትብላ፤ ሆኖም ከካህኑ ቤተሰብ ሌላ ሰው የተቀደሰውን ነገር መብላት የለበትም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነቷ እንደ ነበረች ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ፥ ከአባቷ እንጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ልዩ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ። ምዕራፉን ተመልከት |