ዘሌዋውያን 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ካህኑ ግን ባርያ በገንዘቡ ቢገዛ እርሱ ይብላ፤ በቤቱም የተወለዱት ለእርሱ ከሆነው እንጀራ ይብሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ነገር ግን ካህኑ በገንዘብ የገዛው ወይም በቤቱ የተወለደ ባሪያ ቢኖረው፣ ያ ባሪያ ከካህኑ ድርሻ መብላት ይችላል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ካህኑ በገንዘቡ የገዛው ወይም በቤቱ የተወለደ አገልጋዩ ግን የካህኑ ድርሻ ከሆነው ምግብ ይብላ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ካህኑ ግን በገንዘቡ አገልጋይ ቢገዛ እርሱ ከምግቡ ይብላ፤ በቤቱም የተወለዱት ከእንጀራው ይብሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ካህኑ ግን በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ እርሱ ይብላው፤ በቤቱም የተወለዱት ከእንጀራው ይብሉ። ምዕራፉን ተመልከት |