Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ካህናት አናታቸውን አይላጩ፥ ጢማቸውንም አይላጩ፥ ገላቸውንም በመቁረጥ አይተልትሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ካህናት፥ ለሙታን በማዘን የራስ ጠጒራቸውን አይላጩ፤ ጢማቸውን አሳጥረው አይቊረጡ፤ ፊታቸውንም አይንጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ ሞተው ሰው ራሳ​ቸ​ውን አይ​ላጩ፤ ጢማ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም አይ​ንጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ራሳቸውን አይላጩ፥ ጢማቸውንም አይላጩ፥ ሥጋቸውንም አይንጩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 21:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እናንተ የጌታ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትቦጭቁ፤ የጭንቅላታችሁን ጠጉር አትላጩ፤


ራሳቸውን አይላጩ፥ የተያዘ ጠጉራቸውንም አይልቀቁትም፥ ነገር ግን የራሳቸውን ጠጉር ይከርከሙ።


ደስ ስለምትሰኚባቸው ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ፀጉርሽንም ተቆረጪ፤ መላጣነትሽን እንደ ንስር አስፊ፤ በምርኮ ከአንቺ ተወስደዋልና።


ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።


“ራስ ሁሉ መላጣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና፤ በእጅም ሁሉ ላይ መተልተል በወገብም ላይ ማቅ አለና።


ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፥ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም፥ ስለ እነርሱም ማንም ገላውን አይነጭም ራሱንም አይላጭም፤


በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ፥ ጠጉራችሁን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራችሁ።


ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።


ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ እርሱ እንዳይቈጣ የራሳችሁን ጠጉር አታጐስቁሉ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ጌታ እሳትን ልኮ ስላደረገው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።


በሕዝቡ መካከል ያሚገኝ አለቃ የረከሰ እዳይሆን ራሱን አያርክስ።


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለ ሰይፍ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ለራስህ ትወስደዋለህ፥ በራስህና በጢምህም አሳልፈው፥ ሚዛንንም ውሰድ ጠጉሩንም ትከፋፍለዋለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች