Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 21:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እጅግ ቅዱስ የሆነውን እና የተቀደሰውን የአምላኩን እንጀራ ይብላ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን ምግብ ይብላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንዲህ ያለው ሰው ሁለቱንም ዐይነት፥ ማለትም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የምግብ መባ መብላት ይችላል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የቅ​ዱ​ሱ​ንና የቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳ​ኑን የአ​ም​ላ​ኩን መባ ይብላ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የቅዱሱንና የቅዱሰ ቅዱሳኑን የአምላኩን እንጀራ ይብላ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 21:22
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትንም ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እጅግ የተቀደሰ ነውና ለጌታ ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የተረፈውን የእህሉን ቁርባን ውሰዱ፥ እርሾም ያልገባበት ቂጣ አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤


“እጅግ የተቀደሰ ነውና፥ የሕዝቡንም ኃጢአት እንድትሸከሙ፥ በጌታም ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ለእናንተ ሰጥቶአልና ለምን የኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን በቅዱሱ ስፍራ አልበላችሁም?


የኃጢአትን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርድበት በተቀደሰው ስፍራ ጠቦቱን ያርደዋል፤ እንደ ኃጢአት መሥዋዕቱም እንዲሁ የበደል መሥዋዕቱ ለካህኑ ይሆናል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።


ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና።”


ከእንግዳም ሰው እጅ የተገኙ እንደነዚህ ያሉ እንስሶችን ሁሉ ለአምላካችሁ እንጀራ እንዲሆኑ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።”


ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ነገር ይበላል።


“ነገር ግን ሰው የእርሱ ከሆነው ነገር ሁሉ ለጌታ ለይቶ እርም ያደረገው፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፥ አይቤዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ካህኑም ሰውነቱን ለመሸፈን የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።


ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእርሱ ይበላል፤ እጅግም የተቀደሰ ነው።


“የበደል መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።


ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።


የእስራኤል ልጆች እንደ ስጦታ ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለጌታ ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በጌታ ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ ለዘለዓለም የጨው ቃል ኪዳን ነው።”


በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች