ዘሌዋውያን 21:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 “ለአሮን እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ለማቅረብ አይቅረብ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 “ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከዘርህ የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የእኔን የአምላኩን የምግብ መባ ማቅረብ የለበትም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 “ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ከወገንህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን መባ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። ምዕራፉን ተመልከት |