Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 20:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፥ ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል፤ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ይገደል፤ አባቱንና ወይም እናቱን ስለ ሰደበ ሞት የተፈረደበት በራሱ በደል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ማና​ቸ​ውም ሰው አባ​ቱን ወይም እና​ቱን ቢሰ​ድብ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ሰድ​ቦ​አ​ልና በደ​ለኛ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፥ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፤ ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 20:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት።


ሙሴ፥ አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ፈጽሞ ይሙት ብሎ ነበርና፤


“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር’ ደግሞም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት’ ብሎ አዞአልና፤


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።


በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።


አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማያመሰግን ትውልድ አለ።


ዳዊትም፥ “ ‘ጌታ የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል የገዛ አፍህ መስክሮብሃልና፥ ደምህ በራስህ ላይ ይሁን” አለው።


እግዚአብሔር ይህን ያደረገውም፥ በሰባው የይሩበኣል ልጆች ላይ ስለ ተፈጸመው ግፍና ስለ ፈሰሰው ደማቸው፥ ወንድማቸውን አቤሜሌክና ወንድሞቹን እንዲገድል የረዱትን የሴኬም ሰዎች ለመበቀል ነው።


ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ።


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ደም ጌታ ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የእስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር አዛዥ ዐማሣ ነበሩ።


ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፥ እኛም ንጹሐን እንሆናለን፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን ማንም ሰው እጁን ቢጭንበት ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል።


“ወንድ ወይም ሴት የሙታን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጸመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።”


አንዲት ሴት ወደ ማናቸውም እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።


አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ መጻተኛውን ጨቆኑ፥ በአንቺ ውስጥ የሙት ልጅንና መበለቲቱን አስጨነቁ።


በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፍንም ቢወስድ፥ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፤ እነዚህን ርኩሰቶች ሁሉ አድርጎአልና በእርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በላዩ ላይ ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች