Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 መቅደሴን ለማርከስ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ለማንቋሸሽ ልጁን ለሞሌክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ልጁን ለሞሎክ በመስጠት መቅደሴን አርክሷልና፣ ቅዱሱን ስሜንም አቃልሏልና፣ በዚያ ሰው ላይ ጠላት እሆንበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ማንም ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሌክ አሳልፎ በመስጠት የተቀደሰውን ድንኳኔን ቢያረክስና ቅዱስ ስሜንም ቢያሰድብ፥ ያ ሰው በእኔ ፊት የተጠላ ይሆናል፤ ከሕዝቡም ለይቼ አጠፋዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 መቅ​ደ​ሴን ያረ​ክስ ዘንድ፥ የቅ​ዱ​ሳ​ኔ​ንም ስም ያጐ​ስ​ቍል ዘንድ ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ሰጥ​ቶ​አ​ልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ያጐሰቁል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 20:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከልጆችህ ማናቸውንም ለሞሌክ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ አትስጥ፥ በዚህም የአምላክህን ስም አታርክስ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።


“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።


“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የጌታን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው።


“እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”


ነገር ግን ልጁን ለሞሌክ ሲሰጥ፥ የአገሩ ሕዝብ አይቶ ያንን ሰው ፈጽሞ ቸል ቢለው ባይገድሉትም፥


የሞተውን ሰው በድን የነካ ማናቸውም ሰው ሁለመናውን ባያነጻ የጌታን ማደሪያ ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ ከርኩሰት የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኩሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።


እንደ እርሱ ዓይነት የሚቀምም ሰው ወይም ከእርሱ በሌላው ላይ የሚያፈስስ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።’”


ነገር ግን የረከሰ ሰው ሆኖ ሳለ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ የበላ እንደሆነ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።


ማንም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ምንም ዓይነት ርኩስ ሆኖ የተጠላን ማናቸውንም ርኩስ ነገር ነክቶ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”


በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የአምላካቸውንም ስም አያረክሱም፤ እነርሱም የአምላካቸው እንጀራ የሆነውን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያቀርባሉና የተቀደሱ ይሆናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች