Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 20:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “ስለዚህ እንድትቀመጡባት ወደማመጣችሁ ስፍራ ምድሪቱ አንቅራ እንዳትተፋችሁ ሥርዓቴን ሁሉ፥ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ፥ አድርጉትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ ‘እንድትኖሩባት እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ አድርጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “እኔ እንድትገቡባት የማደርጋት የከነዓን ምድር አንቅራ እንዳትተፋችሁ ሕጌንና ሥርዓቴን ሁሉ ጠብቁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “እን​ግ​ዲህ ትቀ​መ​ጡ​ባት ዘንድ የማ​ገ​ባ​ችሁ ምድር እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንግዲህ ትቀመጡባት ዘንድ የማገባችሁ ምድር እንዳትተፋችሁ ሥርዓቴን ሁሉ፥ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ፥ አድርጉትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 20:22
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፥ በትእዛዜ እንድትሄዱና ፍርዴን እንድትጠብቁ አደርጋችኋለሁ ትፈጽሟቸዋላችሁም።


የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው፥ የጽድቅህም ፍርድ ሁሉ ለዘለዓለም ነው።


በፍጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ፥ ስማኝ፥ ሥርዓትህን እፈልጋለሁ።


እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን።


ፍርዶችህን ሁልጊዜ በመፈለግ ነፍሴ በናፍቆት ደቀቀች።


ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ።


ነፍሴ ትኑርልኝ ታመሰግንህማለች፥ ፍርድህም ይርዳኝ።


ሥርዓትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አወጡ።


ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።


ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዓት፥ ሕጎችም እነዚህ ናቸው።


እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም ባድማ ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ይፈርሳሉ።


ሥርዓቴን ሁሉ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ አድርጉአቸውም፤ እኔ ጌታ ነኝ።”


“በፊታቸው የምታኖረው ሥርዓት ይህ ነው።


ስለ ጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ።


የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች