Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ ‘ማንኛውም ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አጎቱን አዋርዷልና ሁለቱም ይጠየቁበታል፤ ያለ ልጅም ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አንድ ሰው ከአጐቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጐቱን ያዋረደ ስለ ሆነ እርሱም ሆነ ሴትዮዋ ፍዳቸውን ይቀበላሉ፤ ያለ ልጅም ይቀራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰውም ከቅ​ርብ ዘመዱ ሚስት ጋር ቢተኛ የቅ​ርብ ዘመ​ዱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ያለ ልጅ ይሞ​ታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 20:20
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአባትህን ወንድም ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፥ ወደ ሚስቱም አትቅረብ፤ የአጎትህ ሚስት ናት፤


‘መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች፥ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው፤’ የሚባልበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና።


“ጌታ እኔን በተመለከተበት ጊዜ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል አስወገደልኝ።”


ኤልሳቤጥም መካን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”


ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።


ዘርም ትውልድም በሕዝቡ መካከል አይሆንለትም፥ በመኖሪያውም ውስጥ የሚቀመጥ ሰው አይቀርለትም።


ሰውም የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ርኩሰት ነው፤ የወንድሙን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና፥ እነርሱ ልጅ አልባ ይሆናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች