Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 20:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ማናቸውም ሰው ከምራቱ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ደማቸውም በራሳቸው ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ ‘አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ሁለቱም ይገደሉ፤ ነውር አድርገዋልና ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንድ ሰው ከምራቱ ጋር ቢያመነዝር ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤ የሥጋን ዝምድና በዝሙት በማርከሳቸው ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ማና​ቸ​ውም ሰው ከም​ራቱ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ ጸያፍ ነገር አድ​ር​ገ​ዋል፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ማናቸውም ሰው ከምራቱ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ደማቸውም በላያቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 20:12
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፥ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፥ “እባክሽ አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፥ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።


“ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፥ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፥ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች።


ፀሐይ ከወጣችበት ግን ደሙ በላዩ ነው፥ ዋጋውን ይክፈል፤ የሚከፍለው ከሌለው ስለ ሰረቀው ነገር ይሸጥ።


የምራትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የልጅህ ሚስት ናት፤ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።


በእርሱም ራስህን እንዳታረክስ ከማናቸውም እንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ለመተኛት በእንስሳ ፊት አትቁም፤ ጸያፍ የሆነ ተግባር ነው።


“‘ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች